የ2010 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ሞቅ ያለ አቀባበል ተደረገላቸው

የአንደኛ አመት ተማሪዎች በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ የዩኒቨርሲቲው ነባር ተማሪዎች ለአቀባበሉ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ እጅግ በጣም ቤተሰባዊነት በተላበሰ ዲስፕሊን ለእህት ወንድሞቻቸው አቀባበል አድርገዋል፡፡ እነዚህ ነባር ተማሪዎች ሻንጣ በመሸከም፣ በጥዑም ሙዚቃ በማጀብ፣ ማደሪያ ዶርማቸውን በማሳየት እና ሌሎች ለተማሪዎቹ አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት የሚያስደምም ስራ ሰርተዋል፡፡ ይህ አቀባበል ይበጅ፣ ይቀጥል የሚያስብል ነው፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲው አመራርና ሠራተኞች ተገቢውን አገልግሎት ለተማሪዎች በመስጠት አቀባበሉ ያማረ እንዲሆን አድርገውታል፡፡