ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ (ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትነት)

የስራ ማስታወቂያ

በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መመሪያ ደንብ 002/2009 መሰረት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በፕሬዝዳንትነት ቦታ ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

ወዳደሪያ መስፈርት

1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሶስተኛ ዲግሪ ወይም ሁለተኛ ዲግሪ ያለው/ያላት

2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት፣ በኢንደስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በመሪነት ወይም በባለሙያነት ደረጃ ያገለገለ/ች እና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች

3ኛ. በተቋሙ የከፍተኛ ትምህርትን ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ጥራትን ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ተቋማቱን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት የሚያስችል ስትራቲጅካዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፤

4ኛ. የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የቦርድና ሴኔት አባላት እንደሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ የስትራቴጂክ ዕቅዱን በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል

አመልካቾች፡

ይህ ማስታወቂያ በሜዲያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከ5 እስከ 10 ገጽ የሚሆን ስትራቴጅክ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አለምአቀፍና ህዝብ ግንኙነት ቢሮ ቁጥር 15 በአካል ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ግንኙነት ጽ/ቤት (Liaison Office) ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ (Liaison Office) ፡- ሰሚት፣ ዲቦራ ት/ቤት ጀርባ

  • ስልክ ቁጥር 011 639 02 22

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉትን አድራሻዎች መጠቀም ይቻላል፡፡

                    ስልክ ቁ.  +251 911 69 75 88 / +251 25 111 15 01

                    Email:   IPROffice@ddu.edu.et

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመልማይና ምርጫ ኮሚቴ

ዳውን ሎድ፡ የመወዳደሪያ መስፈርቶች ፣ የ2009 አመታዊ ሪፖርት ፣ የዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ ፕላን