ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ምክትል ፕሬዜዳንቶችን ሾመ

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በምክትል ፕሬዝዳንት ቦታዎች ላይ ምልመላና ምርጫ ሲያካሄድ ቆይቷል፡፡ በእዚሁ መሰረት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ በቀን 26/12/2010 ዓ.ም በአደረገው መደበኛ የምርጫና ምልመላ ኮሚቴ የአቀረቡለትን እጩዎች፡

  1. ዶ/ር ኡባህ አደም የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት
  2. ዶ/ር ግርማ ሞገስ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት በማድረግ አጽድቆ ሾሟል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ተሿሚዎቹን እንኳን ደስ አላችሁ እያለ መጪዉ ጊዜ የትጋትና የላቀ ውጤት የምታስመዘግቡበት ዘመን እንዲሆንላችሁ ይመኛል፡፡ ለእዚህ ስኬት የተቋማችን መምህራንና ሰራተኛ ለተሻለ እድገት ከጎናቸው በመሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ቃል ይገባል፡፡