የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት አላማዎች


 • በሙያ ሥነ-ምግባርና በማነጽ የነቃና ሙስና ሊሸከም የማይችል ሠራተኛ እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ፡፡
 • የሙስና ወንጀልንና ብልሹ አሰራርን መከላከል፡፡
 • ሙስናና ብልሹ አሰራሮች እንዲጋለጡና በአጥፊዎች ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ጥረት ማድረግ፡፡

ተጠሪነቱ

 • ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ነው

ዳይሬክቶሬቱ የሚያከናውናቸው ተግባራት

 1. ለዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎችና ሠራተኞች የፀረ-ሙስና ፓሊሲዎች የፀረ-ሙስና ህጐች፣ ደንቦችና መመሪያዎች የመልካም ሥነ-ምግባር ግንዛቤ እንዲዳብር ያደርጋል፡፡
 2. በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ደንቦችና መመሪያዎች መከበራቸውን ይከታተላል፡፡
 3. የሥነ-ምግባር መመሪያ አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር ያዘጋጃል፡፡ ያፀድቃል ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
 4. ለሙስናና ለብልሹ አሰራሮች ቀዳዳ የሚከፍቱ አሠራሮች እንዲስተካከሉ ለጥናት የሚሆን መነሻ ሃሳብ ለፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያሳውቃል፡፡ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትም ያሳውቃል፡፡
 5. የአስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ያማክራል፡፡
 6. የሙስና ወንጀል ስለመፈፀሙ ጥርጣሬ ሲኖረው ለፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሪፓርት ያደርጋል፡፡ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ያሳውቃል፡፡
 7. ብልሹ አሠራሮችና ሙስናን ለማጋለጥ ለሚደረገው እንቅስቃሴ ሠራተኛውን ከቂም በቀል እርምጃ ለመከላከል የሚያስችል ስርዓት በሚዘረጋበት ሁኔታ የዩኒቨርሲቲውን የበላይ ኃላፊ ያማክራል አፈፃፀሙንም ይከታተላል፡፡
 8. የሥነ-ምግባርና ጥሰቶች የሚመለከት ጥቆማዎችን ተቀብሎ በማጣራት የውሳኔ ሃሳብ ለዩኒቨርሲቲው የበላይ ኃላፊ ያቀርባል ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላሉ፡፡
 9. ከባድ የሥነ-ምግባር ጥሰት ተከስቷል ብሎ ካመነ ለፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሪፓርት ያደርጋል፡፡ ለዩኒቨርሲቲው የበላይ ኃላፊ ያሳውቃል፡፡
 10. የሠራተኞች ቅጥር፣ ደረጃ እድገት፣ ዝውውር የዕቃ ወይም የአገልግሎት ግዥን በተመለከተ ደንብና መመሪያ ተጥሷል ብሎ ሲያምን ለዩኒቨርሲቲው የበላይ ኃላፊ ማስተካከያ እንዲደረግ ከአስተያየት ጋር ሪፓርት ያደርጋል፡፡ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
 11. ሠራተኛው ብልሹ አሰራሮችና የሙስና ወንጀሉን በማጋለጥ ሂደት ተጽኖ እንዳይደርስባቸው ይከታተላል፡፡ ተጽዕኖ ያደረገ ወይ የሞከረ ከማስረጃ ጋር ለዩኒቨርሲቲው የበላይ ኃላፊ ሪፓርት ያደርጋል ስለሚወሰደው እርምጃ ይከታተላል፡፡ተፅዕኖ አድራጊው የዩኒቨርሲቲው የበላይ ኃላፊ ሲሆን ለፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያሳውቃል፡፡
 12. በሥነ-ምግባርና በሙስና ዙሪያ ሠራተኛው ወቅታዊ ውይይት እንዲያደርግ የዩኒቨርሲቲውን የበላይ ኃላፊ ያሳስባል፡፡
 13. ኦዲተሮችና የዲሲፕሊን እና የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች የሚያስተላልፉቸውን ሪፓርቶችና ውሳኔዎች የተሰጠባቸው ጉዳዮች ላይ ስለተፈፃሚነታቸው ክትትል ማድረግ፡፡
 14. መልካም ሥነ-ምግባርን በማስፈን ሙስናንና ብልሹ አሰራሮችን ለማዋጋት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ያቀናጃል፡፡
 15. የዓመቱ ዕቅድ የሩብ ዓመትና አመታዊ ሪፓርት አዘጋጀቶ ለዩኒቨርሲቲው የበላይ ኃላፊና ግልባጭ ለፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያሳውቃል፡፡
 16. በኮሚሽኑ በተሰጠው ውክልና መሠረት የተሿሚዎችንና የሠራተኞችን ሀብት መመዝገብና ለኮሚሽኑ ማስተላለፍ፡፡
 17. አግባብ ባለው ህግ መሠረት ተለይተው የሚሰጡትን ሥነ-ምግባርን የሚመለከቱ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ኃላፊነት

 • የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት የሚጠይቃቸውን መረጃዎችና ሌሎች ድጋፎች በመስጠት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
 • ለሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ትብብር መከልከል አስተዳደራዊ ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡

የዳይሬክቶሬቱና የኮሚሽኑ የሥራ ግንኙነት

 • የቴክኒክና የሙያ ዕገዛ ያደርጋል፡፡
 • የጋራ መድረክ በማመቻቸት በተከናወኑና ባጋጠሙ ችግሮች ላይ ይወያያል፡፡
 • በሚቀርቡለት የትብብርና የድጋፍ ጥያቄዎች መሠረት አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ያደርጋል፡፡
 • ስለተሰሩ ሥራዎችና ስላጋጠሙ ችግሮች የሚላኩለትን ሪፓርቶች ይመለከታል፡፡
 • በሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳሬክቴሬት ላይ የቂም በቀልና የበቀል እርምጃዎች እንዳይወሰዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
 • የበቀል እርምጃዎች ከተወሰዱ የበቀል እርምጃው እንዲቆም የእግድ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡
 • የሙስና ወንጀል ሲፈፀም ከፍተኛ የሥነ-ምግባር ጥሰት ተሰራ ተብሎ ሲላክ መመርመርና እርምጃዎች መውሰድ፡፡
 • ሥልጠናዎችን ያዘጋጃል እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

ምንጭ፡-

 • የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች አሰራር የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 144/2000
 • የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 668/2002