የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የጥቆማ አቀራረብ ሥርዓት

ሙስናና ብልሹ አሰራሮች በወቅቱ በሚገቱበት መንገድ ላይ ሥልታዊ በሆነና በተደራጀ መንገድ እንዲወገዱ ካልተደረገ በቀር በአገር፣ በማህበረሰብና በግለሰብ ለይ የሚደርሱትን ጉዳት መገመት አይቻልም፡፡
የተጀመረውን የፀረ-ሙስና ትግል በተጠናከረ መልኩ ለማካሄድም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ጥሩ ሥነ-ምግባርን ለማስፈንና ሙስናን ለመከላከል የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት እንዲዘረጋ ተደርጓል፡፡
እነዚህ በመወሰድ ላይ ያሉ እርምጃዎች ፍሬያማ ሊሆኑ የሚችሉት ህብረተሰቡና የመንግስት ሠራተኞች የሙስና ድርጊቶችን “አያገባኝም” ብሎ ከማየት ባሻገር ነገ በራሳቸውም ላይ ሊደርስ እንደሚችልና በሀገርም ላይ የሚያስከትለውን ችግር ከግንዛቤ በማስገባት ድርጊቶቹን በመጠቆምና በማጋለጥ ሀላፊነታቸውን መወጣት ሲችሉ ብቻ ነው፡፡
የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያለማቋቋም በወጣው ደንብ ቁጥር 144/2ዐዐዐ መሠረት ማንኛውም የሥራ ሀላፊ ወይም ሠራተኛ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን የማጋለጥ ግዴታ ያለበት መሆኑና አለማጋለጥ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑ ተገልዷል፡፡

ጥቆማዎች የሚከተሉትን ነጥቦች ኣካቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

 1. የጠቋሚው ስምና አድራሻ (የግድ አይደለም)፣
 2. የተፈፀመው ድርጊት ምን እንደሆነ፣
 3. የተጠርጣሪው ስም፣ ሙያ ወይም ሥራና የሥራ መደብ፣
 4. ድርጊቱ የተፈፀመበት የሥራ ሂደት፣
 5. ድርጊቱ የተፈፀመበት ጊዜና ቦታ፣
 6. በድርጊቱ የተጠቁሙ ወይም የተጎዱ ሰዎች፣
 7. በድርጊቱ የተገኘ ጥቅም፣
 8. የሚታወቅ ከሆነ የተገኘው ጥቅም የሚገኝበት ቦታ ወይም ሁኔታ፣
 9. የሚታወቅ ከሆነ በተጠርጣሪው ስም ያሉ ቀንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፣
 10. የጉዳቱን እውነተኝነት ሊያስረዱ የሚችሉ የሰነድ ማስረጃዎች፡፡

የጥቆማ አድራሻዎች

 • በአካል መምጣት ለሚፈልጉ አድራሻችን - ፕሬዝዳንት ቢሮ 2ኛ ፎቅ Room 6
 • በኢሜይል፡ eac@ddu.edu.et
 • ክፍሉ ባዘጋጀው የጥቆማ ሳጥኖች ውስጥ
 • በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገፅ Ethics & Anti-Corruption ኦንላይን ማመልከት ይችላሉ

“የሙስና ሰንሰለቶችን እንበጥስ”
“Break the Corruption Chain ”