የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሀገራዊ ስልጠና

Share this story

Posted on: Sep 16,2016

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ለመምህራንና ሰራተኞች በተዘጋጀው ሀገራዊ ሥልጠና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በሰዓቱ በመገኘት ለስልጠና የተዘጋጀውን ዶክመንት በመውሰድ ወደ ተዘጋጀላቸው አዳራሽ ገብተዋል፡፡ የአስተዳደር ሰራተኞች በአንድ የኃይል መድረክ መምህራን በሌላ የኃይል መድረክ ተከፍሎ በተሳካ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡ ለስልጠናው የተመደቡ አሰልጣኞችና አወያዮች በሰአቱ ቦታቸውን በመያዝ ለእለቱ በተያዘው የስልጠና ርዕስ ላይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ለጧት የተያዘው መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡

ከሰዓት በኃላ የቡድን ውይይቱ የቀጠለ ሲሆን የአስተዳደር ሰራተኞች በ15 ቡድን የተከፈሉ ሲሆን መምህራን በ16 በድን ተከፍለዋል፡፡ እያንዳንዱ ቡድን ሁለት አወያይና አንድ ቃለ ጉባኤ ያዥ አላቸው፡፡ ለየቡድኑ አወያዮች አንዱ ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞችና መምህራን የተወከለ ሲሆን ሁለተኛው ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር የተመደበ ነው፡፡ በአጠቃላይ የእለቱ ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡

 

የስልጠናው ተሳታፊዎች በከፊል