የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ኢኮቴ) የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ጥናት ተካሄደ

Share this story

Posted on: Jul 12,2017

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ኢ.ኮ.ቴ ዳይሬክቶሬት እና የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኢ.ኮ.ቴ ዳይሬክቶሬት በአስተዳደሩ ለሚገኙ የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ለተጋባዥ እንግዶች ስለ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ኢኮቴ) የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ጥናት በማዘጋጀት የፓናል ውይይት አደረጉ

አውደ ጥናቱን በእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰይፈዲን አብዱራህማን ዩኒቨርሲቲውና አስተዳደሩ በኢኮቴ ብቻ ሳይሆን በሰው ሃብት ልማትም ተቀናጅተው መስራት መጀመራቸውን ገልፀው በቀጣይ ይህ ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

በአስተዳደሩ በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ኢ.ኮ.ቴ) ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች በጅምር ደረጃ ያሉና በቀጣይ ይበልጥ የሚጠናከሩ ይሆናሉ፡፡ ዋናው ርዕሰ ጉዳያችን ወደሆነው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በኢኮቴ የመቅረፍ ስራን በተመለከተ ግን በርካታ አበረታች ስራዎች እንደተሰሩ አብራርተዋል፡፡

መንግስት ኢ.ኮ.ቴን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ከተቻለ አሁን እየተነሱ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በግማሽ መቀነስ ይቻላል ብሎ ያምናል፡፡ ይህ ከብዙ አቅጣጫ ሊታይ የሚችል ነገር ነው፡፡ የእኛን አፈፃፀም በማየት ብቻ እንኳ ኢኮቴ ምን ያህል የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ በቀጥታና በተዘዋዋሪ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት መረዳት አያዳግትም፡፡

በሌላው በኩል በብሔራዊ የኢኖቬሽን ስርዓት ውስጥ መንግስት ፣ ዩኒቨርስቲዎች ፣ ቴክኒክናሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ፣ የምርምር ማዕከላት እና ኢንዱስትሪዎች ዋነኛ ተዋናይ መሆናቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ እና በዚህ ማዕቀፍ ስር የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲና በፐብሊክ ሰርቪስና ሰውሃብት ልማት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት መካከል በኢኮቴ ዘርፍ ተቀናጅቶ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት በተፈረመው መሠረት ዩኒቨርሲቲው ማህበረሰቡን ሊጠቅሙ በሚችሉ ዘርፎች ሁሉ ከአስተዳደሩ ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት ቁርጠኛ ነው፡፡

በኢኮቴ ዘርፍ የዩኒቨርሰቲ -ማህበረሰብ ትስስርን ጠቀሜታ የሚያሳይ የትምህርትና ስልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ እንደ  መነሻ በማድረግ እንዲሁም በሀገራችን ትስስሩ ያለበት አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ በሚያሣይ መልኩ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርተ ወካይ በሆኑት በአቶ ብርሃነ መስፍን ጥናታዊ ፅሑፍ ቀርቧል፡፡ ይህም በጠንካራ ትብብር ላይ ለተመሰረተና ለተቀናጀ የሳይንስ' ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን አቅም ግንባታ እንቅስቃሴ አጠቃላይ የሆነ የአመራር ማዕቀፍ በመፍጠር ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ ለማሸጋገር ሀገራዊ የቴክኖሎጂ አቅም መፍጠር የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት ሀገር በቀል ዕውቀቶችንና ቴክኖሎጂዎችን ማልማትና ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን እና እንዲሁም በአስተዳደሩ በኢኮቴ ዘርፍ የተከናወኑ እና እየተከናወኑ  የሚገኙትን አበይት ተግባራት አፈፃፀም በአስተዳደሩ በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶተሩ በአቶ አህመድ ሰኢድ ገለፃ ተደርጓል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለው ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተፈራረምነው የኢንዱስትሪ ቀጠናዊ ትስስር የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በቀጣይ የተጀመረውን ቅንጅታዊ አሠራር አጠናክረው እንደ ሚያስቀጥሉ  በመግለጽ ከተሣታፊዎች ሰፊውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ተችሏል፡፡

ከአውደ ጥናቱ በኋላ የማጠቃለያ መዝጊያ ንግግር ያደረጉት እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫን ያመላከቱቱ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና የማህበረሰብ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ መሀዲኢጌ በዩኒቨርስቲው እና በአስተዳደሩ ኢኮቴ ዳይሬክቶሬት መካከል የቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራትን በቅንጅት ለማከናወን የሚያስችል ስርዓት በተዘረጋው መሠረት የዩኒቨርስቲ መምህራንና ተማሪዎች በኢንዱስትሪ ውስጥ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንቅስቃሴ የሚሳተፉበት ሁኔታ ለማመቻቸት በምርምር ተቋማትና በኢንዱስትሪዎች መካከል ቴክኖሎጂን በማላመድ ረገድ የተጠናከረ ትስስር እንዲኖር እንዲሁም ዩኒቨርስቲው አስተዳደሩ ለሚያከናውኗቸው የቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራት የማማከር ድጋፍ መስጠት የሚችሉበትን የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የተጠናከረ ድጋፍ እንደ ሚያደርጉ አሣውቀዋል፡፡