በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመ የዜሮ ፕላን ማእከል ተመረቀ

Share this story

Posted on: Jul 19,2018

በሴቶችና ወጣቶች ኤች አይ ቪ ኤድስና ልዩ ፍላጎት ጽ/ቤት የተቋቋመው የዜሮ ፕላን ማእከል በ23/09/2010 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና ተማሪዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል፡፡ የዜሮ ፕላን ማእከል የተቋቋመው 3 አበይት ጉዳዮችን ታሳቢ አድርጎ ነው፡፡ ይኸውም የሴት ተማሪዎችን የመውደቅ ምጣኔ 0 ማድረስ፣ ፆታዊ ጥቃትን መከላከል እና መቀነስ እንዲሁም የስነ ተዋልዶ ችግሮችን ማስወገድና መከላከልን መሰረት ያደረግ ነው፡፡

አቶ ጌትነት ቶሎሳ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ የመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ይህ ማእከል በግቢው ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች የሚሰጠው ጥቅም ዘርፈ ብዙ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ትኩረት ተሰቶት መሰራት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

በዜሮ ፕላኑ ሴት ተማሪዎች ስለ ስነ-ተዋልዶ ጉዳዮች ፣ ስለ ጾታዊ ጥቃትና ኤች አይ ቪ ኤድስ የተለያዩ በራሪ ፅሑፎችን፣ ጋዜጦች፣ መፅሔቶች እና መጽሐፍትን ማንበብ፣ በቴሌቪዥን ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ ፣ ስለ ስነ-ተዋልዶ እና ስለ ፆታዊ ጥቃት የተለያዩ ፊልሞችና ፕሮግራሞችን መመልከት እና የምክር አገልግሎት መስጠትም ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም ሴት ተማሪዎች ትርፍ ጊዜያቸውን በዚሁ ማእከል በማሳለፍ ልደታቸውንና መሰል ፕሮግራሞችን በማመቻቸት ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ውጪ የሚወጡበትን አጋጣሚ እና ለችግር ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ፣ ከላይ በተጠቀሱት ርእሰ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ባለሙያዎችን በመጋበዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ማመቻቸት እና “ሺቲ ናይት” ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት ከብዙ በጥቂቱ በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው፡፡