በዩኒቨርሲቲያችን ምንም የተከሰተ ችግር የለም

Share this story

Posted on: Nov 27,2018

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ2011 ዓ.ም ነባር ተማሪዎችን ጥቅምት 9-11/2011 ዓ.ም እንዲሁም አዲስ ተማሪዎችን ከጥቅምት 15-18 /2011 ዓ.ም ድረስ ተቀብሎ ሠላማዊ መማር ማስተማሩን ከጀመረ አንድ ወር ሆነው፡፡ በእዚህ ጊዜ ውስጥ በዩኒቨርሲቲያችን ምንም የተከሰተ ችግር የለም፡፡ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች ያላቸውን ማናቸውንም ጥያቄ እጅግ በጣም ዲስፕሊን በተሞላበት ሁኔታ ከሚመለከተው አካልና ከከፍተኛ አመራሩ ጋር እየተነጋገሩ እራሳቸውንም የመፍትሔ አካል በማድረግ ሠላማዊ የሆነ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡  

ውድ ተማሪዎቻችን በመካከላቸው ያለውን ወንድማማችነትና እህትማማችነት በጠንካራ አንድነትና ፍቅር በማስተሳሰር ለመጡበት አላማ እንደሚተጉ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ያረጋግጥልናል፡፡ ለእዚህም ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎቻችን አድናቆቱንና ምስጋናውን ያቀርባል፡፡